አባት ፕሬዝዳንት ልጅ ምክትል ፕሬዝዳንት እና ዘራፊ

Sharing addisinformer is caring!

የኢኳቶሪያል ጊኒ ፕሬዝዳንት ልጅ ቴዎዶሮ ንጉኤማ ኦቢያንግ ማንጉኤ የአገሪቱ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር እና የደህንነት ሃላፊ በመሆን በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ ስለዚህ አባት ፕሬዝዳንት ልጅ ደግሞ ምክትል ፕሬዝዳንት ናቸው፡፡

ሆኖም የ47 ዓመቱ ልጅ ሰሞኑን ከፈረንሳይ መንግስት የህዝቡን ገንዘብ ዘርፎ የራሱን ህይወትን አበልጽጓል በሚል ክስ ተመስርቶበታል፡፡

በነዳጅ ሃበቷ የምታወቀው ኢኳቶሪያል ጊኒ አብዛኛው ህዝቧ ከድህነት በታች ሲኖር ኦቢያንግ ግን የተንደላቀቀ ኑሮ እየገፋበት ነው፡፡

በተለይም በድፍረት የቅንጦት ኑሮ በሚል በትዊተር አካውንቱ ላይ ተንደላቀቀ ኑሮውን የሚያሳይ ፎቶ መለጠፉ ነገሩን አስገራሚ አድርጊታል፡፡

የ75 ሺህ ዶላር ተሸከርካሪ፤ የ44 ሺህ ዶላር ዘመናዊ ሞተር፣ 6 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ 15 ዘመናዊ መኪኖች፣ የ24 ሚሊዮን ብር ስዕል፣ እንዲሁም የማይክል ጃክሰን የተለያዩ አልባሳትን በጨረታ በመግዛት የራሱ አድርጓል፡፡

ይህን ከግምት በመሳገባት ነው የፈረንሳይ መንግስት ልጁን የከሰሰው፡

Sharing addisinformer is caring!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *