ሁለት ግለሰቦች ጨረቃን ሊዞሩ ነው

Sharing addisinformer is caring!

በግለሰቦች የሚተዳደረው ስፔስ ኤክስ ጨረቃን ለመዞር ሁለት ግለሰቦች ክፍያቸውን ማጠናቀቃቸው ተገለጸ፡፡

በ2018 ለሚደረገው ጉዞ ቱሪስቶቹ ከወዲሁ ብዙ ገንዘብ ማስቀመጣቸውን የስፔስ ኤክስ ዋና ስራ አስፈጻሚ ኤሎን መስክ ተናግረዋል፡፡

ይህም ከ45 ዓመታት በኋላ ሰዎችን ወደ ሩቁ ስፔስ ለመውሰድ በር ይከፍታል፡፡

ሁለቱ ስማቸው ያልተጠቀሰው ተጓዦች ዘንድሮ በሰው አልባ ጉዞ ሙከራ ከተደረገ በኋላ እንደሚጓዙ አስታውቀዋል፡፡

ጉዞው ውጤታማ እንዲሆን ደግሞ ኩባንያው ከናሳ ጋር ጥሩ ስራ ማከናወኑን ኤሎን አስታውቀዋል፡፡

ጉዞው ጨረቃን በመዞር ብቻ የሚወሰን ሲሆን ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ ይከናወናል ተብሏል፡፡

Sharing addisinformer is caring!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *