ለሌላ በሽታ ይሰጥ የነበረ መድሃኒት ለማይግሬን ይሆናል ተባለ

Sharing addisinformer is caring!

ማይግሬይን ለሚባለው ከፍተኛ የራስ ምታት በሽታ የሚሆን መድሃኒት የማግኘት ትልቅ ተስፋ እንዳላቸው ተመራማሪዎች አስታወቁ፡፡
እንደተመራማሪዎቹ ከሆነ ለማይግሬይ የሚሆነው መድሃኒት አዲስ ሳይሆን ላይሪካ የተባለውና ጥቅም ላይ እየዋለ የሚገኝ መድሃኒት ነው፡፡

ላይሪካ በዋናነት ለሚጥል በሽታ መድሃኒትነት ነበር ለህሙማን ሲሰጥ የቆየው፡፡

መድሃኒቱ የካልሲም መጠንን በመጨመር የራስ ምታትን በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሳል ተብሏል፡፡

መድሃኒቱ ማይግሬን ከመነሳቱ በፊት የሚኖር አነስተኛ መንቀጥቀጥን በማቆም ነው ችግሩን የሚፈታው፡፡

ላይሪካ በማይግሬይን ላይ ያለው ውጤታማነት እስካሁን በቤተሙከራ ውስጥ ባሉ አይጦች ላይ ተሳክቷል፡፡

Sharing addisinformer is caring!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *