የኦስካር አሸናፊዋ ቫዮላ ታሪክ ሰራች

Sharing addisinformer is caring!

ፌንስስ በተሰኘ ፊልሟ ምርጥ ረዳት ተዋናይት በመባል የኦስካር ሽልማትን ያገኘችው ቫዮላ ዴቪስ አዲስ ታሪክ አስመዘገበች፡፡

በፊልም መድረክ የሚሰጡ የተለያዩ ሽልማቶችን ጠራርጋ የወሰደች ጥቁር ተዋናይት በመሆን ነው ታሪክ ሰራችው፡፡

ቫዮላ ከኦስካር በተጨማሪ የኤሚ፣ ቶኒ፣ ጎልደን ግሎብ፣ ኤስ ኤ ጂ እና ቢ ኤ ኤፍ ቲ ኤ ሽልማቶችን ጠራርጋ ወስዳለች፡፡

ቫዮላ ከዚህ በተጨማሪም በብዙ ሽልማቶች ላይ ዕጩ ሆና በመቅረብ ታሪክ ለመስራት ችላለች፡፡

ሃው ቱ ጌት አዌይ ዊዝ መርደር በሚለው ስራዋ ነው ቫዮላ የኤሚን ሽልማት ያገኘችው፡፡

ተዋናይቷ በ2001 እና በ2010 ነው የቶኒ ሽልማትን ያገኘችው፡፡

 

 

Sharing addisinformer is caring!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *