በ700 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው ኢዛና የወርቅ ፋብሪካ የሙከራ ምርት ጀመረ

Sharing addisinformer is caring!

በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን በአስገደ ጽምብላ ወረዳ በ700 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው ኢዛና የወርቅ ፋብሪካ የሙከራ ምርቱን ማምረት ጀመረ።

የፋብሪካው ሥራ አስኪያጅ አቶ ጸጋይ አሰፋ ለኢዜአ እንደተናገሩት፣ ፋብሪካው ከተያዘው ወር መግቢያ ጀምሮ የማምረት ሥራውን የጀመረው የማሽነሪዎችና የኤሌክትሪክ ኃይል ተከላ ሥራውን ካተጠናቀቀ በኋላ ነው።

ፋብሪካው በመስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግ በ700 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባ ሲሆን በመጪው ሚያዚያ ወር ላይ በሙሉ አቅሙ የማምረት ሥራውን ይጀምራል።

እንደ አቶ ፀጋይ ገለጻ፣ ፋብሪካው  በቀን አራት ነጥብ አምስት ኪሎ ግራም ወርቅ የማምረት አቅም አለው።

በየቀኑ ከሚመረተው የወርቅ ምርትም ከአራት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅም ጠቁመዋል።

ለፋብሪካው የወርቅ ግብአት በአካባቢው ከሚገኘው የተፈጥሮ ሃብት ክምችት የሚገኝ መሆኑንም አመልክተዋል።

ፋብሪካው በግንባታ ወቅት ለ200 ሰዎች ጊዜያዊ የሥራ ዕድል ፈጥሮ እንደነበር ያስታወሱት ሥራ አስኪያጁ በቀጣይ ሙሉ ለሙሉ ማምረት ሲጀምር 200 ሰዎችን ቋሚና ጊዚያዊ የሥራ ዕድል ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

በፋብሪካው ውስጥ የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ከሆኑ ወጣቶች መካከል ወጣት ዮሐንስ ሰለሞን  በተማረበት ሙያ የሥራ ዕድል በማግኘቱ ተጨማሪ የተግባር ዕውቀት ለመቅሰም እንዳስቻለው ተናግሯል።

“ፋብሪካው በአገሬ ሰርቼ ለመለወጥ ያለኝን ፍላጎት ይበልጥ አሳድጎልኛል” ብሏል።

በፋብሪካው ውስጥ በመካኒክ የሥራ ዘርፍ የተሰማራው ወጣት ክፍሎም ጊደይ በበኩሉ፣ በተፈጠረለት የሥራ ዕድል ደስተኛ መሆኑን ተናግሯል።

ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ ማምረት እንዲጀምር የፋብሪካው ሠራተኞች ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ በሙሉ ተነሳሽነት እየሰሩ መሆናቸውን አመልክቷል።

በፋብሪካው ግንባታ ወቅት ከውጭ ዜጎች ጋር አብሮ ለመስራት ዕድል ማግኘቱ  የእውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ለማግኘት እንዳስቻለው ገልጿል፡፡

 

Sharing addisinformer is caring!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *