በ 99 ዓመታቸው እስር ያስደሰታቸው አሮጊት

Sharing addisinformer is caring!

ቢጅሜገን የሚገኙ የሆላንድ ፖሊሶች በፌስቡክ ገጻቸው ላይ በእስር ላይ የሚገኙ የአንዲትን አሮጊት ፎቶ ለጥፈው ታይተዋል፡፡

አሮጊቷም ቢሆኑ ያለምንም መሳቀቅ በእጃቸው ላይ ያለውን ካቴና ለካሜራው ሲያሳዩ ይታያል፡፡

የ99 ዓመቷ አሮጊት የታሰሩት ከመሞታቸው በፊት እጃቸው በካቴና ታስሮ እስር ቤት ለመግባት ያላቸውን ፍላጎት ለማሳካት ነው፡፡

በዚህም አና የተባሉት አሮጊት በተዘጋጀላቸው እስር ቤት ውስጥ እጃቸውን በካቴና ታስረው ሲቀመጡ ደስተኛ ሆነዋል፡፡

አና መቼም ቢሆን ቀኑን እንደማይረሱት እምነታቸው መሆኑን ፖሊሶች ተናግረዋል፡፡

የአሮጊቷ ፎቶ በከፍተኛ ሁነታ የተሰራጨ ሲሆን ፖሊሶቹም የአሮጊቷን ፍላጎት ለማሟላት ላደረጉት ሙከራ ምስጋና ተችሯቸዋል፡፡

Sharing addisinformer is caring!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *