ዩ2 ከ25 ዓመታት በኋላ ክስ ተመሰረተበት

Sharing addisinformer is caring!

ታዋቂው የሮክ ባንድ ዩ2 ከ25 ዓመታት በኋላ የሰው ሙዚቃ ካለፍቃድ በመስራት ክስ ተመሰረተበት፡፡

ባንዱ ክስ የተመሰረተበት ፖል ሮዝ በተባለ እንግሊዛዊ የጊታር ተጫዋችና ጸሃፊ መሆኑ ታውቋል፡፡

ፖል ከዚህ ቀደም በአለበም ደረጃ ሊሰራው አቅዶ የተወውን የጊታር ሙዚቃ ዩ2ዎች መጠቀማቸውን ጠቅሶ ነው ክስ የመሰረተው፡፡

የጊታር ተጫዋቹ ዩ2ዎች ሙዚቃውን ዘ ፍላይ በሚለው ዘፈናቸው ውስጥ አካተዋል በሚል ነው የቅጂ መብቱ እንዲጠበቅለት የከሰሰው፡፡

ፖል ለምን ክሱን 25 ዓመት ድረስ እንዳቆው ግን ምንም የሚታወቅ ነገር የለም ተብሏል፡፡

ለጉዳት ካሳው ይሆን ዘንድም 5 ሚሊዮን ዶላር ዩ2ዎች እንዲከፍሉት ጠይቋል፡፡

 

 

Sharing addisinformer is caring!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *