ብዙ ንቅለ ተከላ ያካሄደው ግለሰብ

Sharing addisinformer is caring!

አዳም አልደርሰን የተባለ ግለሰብ እጅግ አደገኛ የሚባሉ ብዙ ንቅለ ተከላዎች በማድረግ በህይወት የተረፈ አራተኛው ሰው ሆነ፡፡

የሰሜን ዮክሻየሩ የ37 ዓመት ጎልማሳ በአንድ ወቅት ለመሞት ሳምንት የሚያህል እድሜ ብቻ እንደቀረው ተነግሮት ነበር፡፡

አልደርሰን ለ17 ሰዓታት ቆ የዕጢ ማውጣት ቀዶ ጥገና ማድርግ ተገዶ ነበር፡፡

30 ሰዎች ተሳተፉበት ቀዶ ጥገና ላይ ሃኪሞች በፈረቃ ነበር ቀዶ ጥገናውን ያከናወኑት፡፡

በዚህም ሆዱን፣ ትንሹን አንጀቱን፣ ትልቁን አንጀቱን፣ ጣፊያውን ጨምሮ የተወሰነውን ሳምባና ሌሎች አምስት ሰውነቱን ክፍሎች አስወጥቷል፡፡

ከዘህ በኋላ ደግሞ እነዚህን 10 የሰውነት አካላቶቹን በንቅለ ተከላ ከሌሎች ሰዎች እንዲተከሉለት ሆኗል፡፡

አሁን አልደርሰን ችግሩን አልፎ ሚስት አግብቶ በሰላም በመኖር ላይ ይገኛል፡፡

 

 

Sharing addisinformer is caring!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *