ጃፓኖች አይተኙም ተባለ

Sharing addisinformer is caring!

ጃፓኖች አይተኙም ይለናል ቢቢሲ፡፡ ይህንን ሁሉም የሚመሰክር ሲሆን በተለይ ጃፓናዊያን የሚያምኑት ነው፡፡

እውነታው ግን ይህ አይደለም፡፡ በተለይ እ.አ.አ በ1980ዎቹ ጃፓን ከፍተኛ የኢኮኖሚ ዕድገት ባስመዘገበችበት ወቅት የሀገሪቱ ዜጎች ከመተኛት ይልቅ ለስራ ቅድሚያ መስጠት ጀምረው ነበር፡፡ በዚህም ዜጎቿ ጠንካራ ሰራተኛ ለመሆን ካላቸው ፍላጎት የተነሳ እንቅልፋቸውን ያጣሉ፡፡ ሁሌም ፕሮግራማቸው በስራና እና በስራ ቀጠሮዎች የተሞላ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አልጋ ላይ መተኛት እንደስንፍና ምልክት ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ በዚህም የስራ ስዓታቸውን ከፍ ለማድረግ ማታ አምሽቶ መተኛትና በለሊት መነሳትን ያካትታል፡፡ ይህን ለማካካስም በትራንስፖርት ውስጥ መተኛት ወይም ናፕ መውሰድ በጃፓን የተለመደ ነው፡፡ ሰዎች ኮሪደር ላይ፣ በአውቶብስ መጠበቂያ ቦታ፣ ባቡር ውስጥ እና በሌሎች ቦታዎች ተኝተው ሊያዩ ይችላሉ፡፡ እናም ለዚህ ነው ጃፓኖች አይተኙም የተባሉት፡፡

Sharing addisinformer is caring!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *